arrow_back Back to News Jun 06, 2026

በጠፋ ሊብሬ ምትክ ለማውጣት

Source: አልተር | Alter

በጠፋ ሊብሬ ምትክ ለማውጣት

ከባለጉዳይ የሚጠበቅ

አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ፤
አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
ሊብሬው ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ፤
ተገቢውን ክፍያ እና ሂደት በመፈፀም ሊብሬው ስለመጥፋቱ በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ማስወጣት፤
ማስታወቂያው አየር ላይ ለ15 ቀን ከቆየ በኋላ ጋዜጣውን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማቅረብ፤
የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።