ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
መኪናው ተመዝግቦ ካለበት ፅ/ቤት የዝውውር ቅፅ ተሞልቶ በፖስታ ታሽጎ ለተቀባይ ፅ/ቤት በፖስታ ማስላክ
አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
ተሽከርካሪውን ለፅ/ቤቱ ባለሙያ እይታ በአካል ማቅረብ፤
የተሽከርካሪውን ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ /ታርጋ/ ማስረከብ፤
ለአገልግሎት ተገቢውን ክፍያ መፈፀም፤
ምትክ ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ /ታርጋ/ መረከብ።
ማስታወሻ
ፖስታው ከመላኩ በፊት የዝውውር ጥያቄው በትክክለኛ የዝውውር ቅፅ መሞላቱን ማረጋገጥ፤
የተቀባይ ፅ/ቤት ትክክለኛ የፖስታ አድራሻ መሆኑን ማረጋገጥ፤
የፋይል ዝውውር ቅፁ ከተሞላ ስድስት ወር ከሞላው ቅፁ ተቀባይነት ስለማይኖረው ቅፁ በተሞላ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቀባይ ፅ/ቤት በመቅረብ ጉዳዩን ማስፈፀም፤