Source: SDS Safety & Driving Skills
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ፥ " ከያዝነው ዓመት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ይጀመራል " ሲል አሳወቀ። የብቃት ምዘናውን መስጠት ያስፈለገው 83 በመቶ በሀገሪቱ እየደረሰ የሚገኘው የትራፊክ አደጋ ከአሽከርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው ብሏል። ይህን ተከትሎም በዚህ ዓመት ምዘናው ሥራ ላይ ባሉ አሽከርካሪዎች እንደሚጀመር አረጋግጧል። በዚሁ መሠረት በሕዝብ እና ደረቅ ጭነት ከ1 እስከ 3 ባሉ ደረጃዎች እንዲሁም ለፈሳሽ 1 እና 2 አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና እንደሚሰጥ ተገልጿል። የሙያ ብቃት ምዘና ከመሰጠቱ በፊት ለአሽከርካሪዎቹ የሙያ ስልጠና...